Saturday, November 28, 2020

በራያ ግንባር የተሰለፈው የመከላከያ ሰራዊታችን በሚያከናውነው የህግ ማስከበር ተልዕኮ ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እየተጋተ የሚገኘው የጁንታው ቡድን የማይደፈረውን ነገር ፈጽሟል ።

በራያ ግንባር የተሰለፈው የመከላከያ ሰራዊታችን በሚያከናውነው የህግ ማስከበር ተልዕኮ ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እየተጋተ የሚገኘው የጁንታው ቡድን የማይደፈረውን ነገር ፈጽሟል ።





የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይል አባላት በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ አረመኔያዊ ተግባር ፈፅሟል ።አቶ በሀይሉ በርኸ " ቤተ ክርስቶያን ውስጥ የመድፍ ጥይት እና ቢ ኤም መሳሪያ አምጥተው አስቀመጡ ፡፡ ለምን ስንላቸው ቤተክርስትያኑ አይመታባችሁም ከተመታም የጥይት ሳጥን እንሰጣችሁና እሱን ሸጣችሁ ታስጠግኑታላችሁ አሉን " ብለዋል ።አቶ በሀይሉ ፣ ቤተ ክርስትያኑ ፈርሷል ውስጡ ያለው ፅላትም ይኑር አይኑር የምናውቀው ነገር የለም ፥ ወያኔ ለሃይማኖት እኩልነት እቆማለሁ ሲል የነበረ ድርጅት ዛሬ ግን ስጋወደሙ የምንቀበልበትን የእምነት ቦታ አርክሶብናል ሲሉ በሃዘንና በቁጭት ስሜታቸውን አጋርተውናል ።





በየትኛውም ፖለቲካዊ እይታ ህዝብን ያልያዘ ሃይል የድል ባለቤት ሊሆን አይችልም ፡፡ ከሞቱ መቃብር አፋፍ ላይ የሆነው ትህነግ ፣ ግን በራሱ ልክ በተሰፋው የሴራ ፖለቲካ ተተብትቦ በሰው ህሊና ሊፈፀሙ አይደለም ሊታሰቡ የማይችሉ ተግባራትን ከመፈፀም አልቦዘነም ።ለሁሉም በመላው ህዝባችን ድጋፍ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት ዘራፊውና ከሃዲው ቡድን ያለችው የተስፋ ጭላንጭል ተሟጣ የመኖር ጀንበሩ ልትጠልቅ አጭር እድሜ ብቻ ቀርተውታል ።አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )ፎቶግራፍ ብርሀኑ ወርቁ





No comments:

Post a Comment

Most Recent

Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced

  Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced Accordingly the following are winning numbers for Admas Digital Lottery 19t...