Tuesday, December 1, 2020

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ሰጡ





የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡





ወ/ሮ ኬርያ የሕወሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግሥት ውስጥም ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት የነበራቸው ናቸው።





ቀደም ሲል የጁንታው ጥቅም ይበልጥብኛል ብለው ወደ መቀሌ ሸሽተው የነበረ ሲሆን አሁን በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት ሰጥተዋል፡፡





ወደ መቀሌ ሲሄዱ አድርሷቸው የነበረው ሾፌራቸው በወቅቱ የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ መኪናውን ይዞ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።





ሌሎችም የሕወሓት አመራሮች እንደ ወ/ሮ ኬርያ በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪውን አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment

Most Recent

Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced

  Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced Accordingly the following are winning numbers for Admas Digital Lottery 19t...