Wednesday, November 25, 2020

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊነት በሚከናወኑ ተግባራት የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የቅሬታ መቀበያ ስልክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊነት በሚከናወኑ ተግባራት የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የቅሬታ መቀበያ ስልክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡





በህወሀት ፅንፈኛ እና እብሪተኛ በሆነው ጁንታው ቡድን ላይ መንግስት የሚወስደውን ህግን የማስከበር እርምጃን ተከትሎ በከተማችን አዲስ አበባ የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች ሊያስከትሉት የሚችሉትን ጥፋት ለመከላከል የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ባደረገው በጥናት ላይ በተመረኮዘ አሰሳና ፍተሻ በርካታ ውጤቶች እየተገኙ መጥተዋል፡፡





ሆኖም በስራ አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ ከህብረተሰቡ የሚመጡ አስተያየቶችና ቅሬታዎች በመኖራቸው መረጃዎችን ለመቀበል ቁጥሩ 011 -8-69-45-02 የሆነ ስልክ መዘጋጀቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባስተላለፈው መልዕክት የሚከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ተገቢ ያልሆነ ጫና በአጠቃላይ ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተገናኙ ማንኛውም አይነት ቅሬታዎች አሉኝ የሚል ነዋሪ በ 011-8-69-45-02 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚችል የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡






https://www.facebook.com/Addisababapolice/posts/2726006680981237

No comments:

Post a Comment

Most Recent

Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced

  Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced Accordingly the following are winning numbers for Admas Digital Lottery 19t...