Tuesday, December 1, 2020

ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሠቆጣ ገቡ

ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሠቆጣ ገቡ






ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች በጁንታው ኃይል ታግተው የነበሩ 1 ሺህ 240 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ዋግኸምራ ዞን ሠቆጣ ከተማ ገብተዋል።
የሠራዊት አባላቱ ከህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከ 8 ሰዓት ጀምሮ እስከ ትላንት ማታ 12 ሰዓት ድረስ ነው ወደ ሠቆጣ የገቡት።
የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ሠቆጣ ለመግባት በርካታ ውጣ ውረድ ማለፋቸውንም ገልጸዋል።
በተለይም የተከዜን ኮሪደር ተከትለው በቀን እና በሌሊት የእግር ጉዞ እንዲሁም ወንዝና ጫካ እያቆራረጡ ሠቆጣ መግባታቸውን የሠራዊቱ አባላት ተናግረዋል።
የአካባቢው አስተዳደር ለሠራዊቱ የምግብ እና የህክምና አቅርቦት ማመቻቸቱም ተመልክቷል።





#EBC

No comments:

Post a Comment

Most Recent

Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced

  Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced Accordingly the following are winning numbers for Admas Digital Lottery 19t...