Thursday, November 26, 2020

ለመሆኑ ትህነግ ኢትዮጵያችን ካሏት ጀግና ክ/ጦሮች ውስጥ 21ኛን መርጦ ሙሉ በሙሉ ለምን ደመሰስኩ አለ ?

ለመሆኑ ትህነግ ኢትዮጵያችን ካሏት ጀግና ክ/ጦሮች ውስጥ 21ኛን መርጦ ሙሉ በሙሉ ለምን ደመሰስኩ አለ ?





ሕዳር 18 ቀን 2013





21ኛ ጉና ክ/ጦር ከሃገራዊ ለውጡና ከሃገር ከሃዲዎች የመቀሌ መመሸግ ማግስት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደ ቀደመ ሰላሙ ለመመለስ ፣የትህነግ ታናሽ ወንድም ኦነግ ሸኔን እግር በእግር ተከታትሎ አፈር ድሜ ያበላና ለአካባቢው ህዝብ እፎይታን የሰጠ ጀግና ክ/ጦር ነው ።





ዛሬም መንግስት ህግን ለማስከበርና የዘመናት የህዝቦችን ጥያቄ ለመፍታት ተገዶ በገባበት ጦርነት ውስጥ ትውልድ የሚሻገር ገድል በራያ ግንባር ተሰልፎ በመስራት ላይ ይገኛል ። ከቆቦ ጀምሮ ያለውን ፈታኝ የመሬት ገፅ በማለፍ የጠላትን መቃብር ያፋጠነ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ጀግና ክ/ጦር ነው - 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር !





ትህነግ ለአመታት የገነባቸው ኮንክሪት ምሽጎችን ለጠላት እንኳን ግርምትን በሚፈጥር ቅፅበት አመድ ሆነዋል - በ21ኛ ።





መሬት ላይ ተቀብረው ለተኩስ አገልግሎት ሲውሉ የነበሩ በርካታ ታንኮች ከስራ ውጪ ሆነዋል። በአካባቢው የነበረው ታጣቂም ከጥቅም ውጪ ሆኗል ። የሚተማመንበት ኮንክሪት ምሽግ እንኳን ፊቱን አዙሮበታል ።





ከከበባቸው ኢትዮጵያዊ እውነት ይልቅ የውስጥ ፍላጎታቸውን ይዘባርቃሉ። እናም ለዚሁ ውሸታቸው ማልበሻ ይሆን ዘንድ በጀግንነቱ ወደር የማይገኝለትን ክፍለ ጦር ደመሰስን ከሚል ህልማቸው ጋር ተጣብቀዋል።





የሆነው ሆኖ ክ/ጦሩ አስቸጋሪ ምሽጎችን በመስበር፥ በርካታ የጠላት ጦርን ከስራ ውጪ በማድረግ ፥ ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ላይ ይገኛል ።





የ21ኛ ክ/ጦር 3ኛብርጌድ አዛዥ ኮ/ል ተክሉ ውሪሳ ° ክፍለ ጦራችንን ደመሰስናቸው ካሉን ሃይሎች ጋር በቅርብ ቀን መቀሌ ላይ እንገናኛለን ። የጀግኖችን የሃይል ምት መቋቋም ያቃተው የከሃዲው ቡድን ሃይል በዛሬው እለት ብቻ ከ300 በላይ ላውንቸርና ብዛት ያላቸው ድሽቃዎችን ጥሎ ነው የፈረጠጠው" ብለዋል።





የ21ኛ ክ/ጦር 3ኛብርጌድ 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ሻምበል ሲሳይ ተሾመ " ለትህነግ ውሸት አዲስ ነገር አይደለም ። ኢትዮጵያውያንን ለበርካታ አመታት ሲዋሽና ሲዘርፍ የነበረ ቡድን ነው። ይህ ደግሞ ለእርሱ የሞቱን መፍጠን ፣ ለእኛ ደግሞ የድላችን መድመቅ ማሳያ መስታወታችን ነው" ብለዋል ።





ም/አስር አለቃ ዋሲሁን አበበ " መሬት ላይ ያለው እውነት በጣም የተለየ ነው። ይሰበራሉ ተብለው የማይታሰቡ ኮንክሪት ምሽጎች በማይታመን ጀግንነት ተሰብረዋል።ይሄን መቋቋም ያቃተው ከሃዲው ቡድን ከመዋሸት ውጪ አማራጭ እንዳይኖረው አድርገን ቀብረንዋል"ብሏል።





ም/አስር አለቃ ሃዊ ረጋሳ" የተሸነፈ ብዙ ያወራል። እኔ የ21ኛ ክ/ጦር ሃኪም ነኝ። ከቀላል ቁስለኛ ውጪ ይህ ነው የሚባል ከባድ ጉዳት አላየሁም።ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነት ከጠላት አፍንጫ ስር ነው ያለው ። ጠላትን በቁጥጥር ስር አውለን ለህዝባችን እስከምናስረክብ ድረስ ፈጣን ጉዟችን አይገታም " ብሏል።





FDRE Defence Force

No comments:

Post a Comment

Most Recent

Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced

  Admas Digital Lottery 19th round winning numbers are announced Accordingly the following are winning numbers for Admas Digital Lottery 19t...